በመንፈስ ተሞሉ/ መንፈስ ይሙላባችሁ ኤፌሶን 5:18
አወያይ ወንድም ጌታቸው ሰው ማደሪያ ነው ለባዶነት ሳይሆን ለሙላት ተፈጥሮአል ። ሰው በፈቃዱ ቤተመቅደስ ለመንፈስ ቅዱስ ወይም ተራ ማደሪያ ከአለም ከሰይጣን ከስጋ ለሚመነጩ ነገሮች ይሆናል። በመንፈስ መሞላት ምንድን ነው? ዮሐንስ 4:24 ሉቃስ 4:17-19 መቀባት መሞላት ለምን? 1 ጴጥሮስ 1:15-16 | 2 ጴጥሮስ 1:5-8 እርሱን እንድንመስለው ሐዋ. ሥራ 1:8 ለመመስከር 1 ቆሮንቶስ 12:7 መንፈስ ቅዱስን ለመግለጥ 1 ተሰሎንቄ 5:23 - እንድንቀደስና ያለነቀፋ እንድንሆን 1 ቆሮንቶስ 12:9-11 በስጦታዎች ለማገልገል ገላትያ 5:22-23 ፍሬ እንዲኖረን ዮሐንስ 14:17 እንድናውቀው መሞላት እንዴት? 1 ቆሮንቶስ 2:11 መንፈስ ከመንፈስ ጋር ህብረት በማድረግ ራዕይ 3:20 የልብን በር መክፈት ወይም ፈቃደኛ መሆን ዮሐንስ 7:37-39 ወደ እርሱ በንስሀ መምጣት ማመን መቀበል መሞላት መቸ? ኤፌሶን 5:18 ሁልጊዜ የመሞለት ውጤቱ በጥቂቱ ሐዋ. ሥራ 2:4 አንደበት በመንፈስ ቁጥጥር ስር ሐዋ. ሥራ 4:31 ቃሉን ያለፍርሀት መግለጥ ኤፌ 5:19-20 ምስጋና ዜማ ቅኔ ሮሜ 8:16 መንፈስ ቅዱስ ለመንፈሳችን በመመስከሩ ፊልጵስዩስ 2:13 መፈለግንም ማድረግንም እንድንችል ማድረጉ በረከት ይብዛላችሁ! የድል ህይወት እግዚአብሔር አብ የሰጠን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተገለጠ፤ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የሚኖር ህይወት ነው::
አብ ሰጠን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድልንሁል ጊዜ ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ድል የእግዚአብሔር ስጦታ ነው 1ኛ የዮሐንስ መልእክት1፥1 ጌታ ኢየሱስ ተገለጠ ፩) ተገለጠ የዳቢሎስን ስራ አፈረሰ የዮሐንስ ወንጌል 16:33 ፪) ሃጢያትን ኮነነልን ሮሜ 8፤3 ፫) ከሃጢያት ነጻ አወጣን 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:9 ፬) በደሙ ህሊናችን አነጻልን ወደ ዕብራውያን 9:14 ፭) ስልጣን አገኘን የሉቃስ ወንጌል 10:20 የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በመንፈስ ሙላት የሚኖር ህይወት የድል ህይወት መሆኑን ባለፈው ጊዜ አይተናል። በመንፈስ ተመላለሱ፥ ገላትያ 5:16፤ የጌታ መንፈስ እርዳታ ሮሜ 8:26 በድል የሚኖሩ ደቀ መዝሙሮች ፩) አለምን ያሸነፈው እምነታችን 1ኛ ዮሐንስ 5:4-5 ፪) በጌታ መኖር 1ኛ የዮሐንስ 2:22-24 ፫) ፍቅርን አውቀን በፍቅር መኖር 1ኛ ዮሐንስ 3:16-24 ፬) ፍቃደኛ መሆንና መታዘዝን ትንቢት ኢሳይያስ 1:19-20 ፭) በመንፈስ መመላለስ/መመራት ወደ ገላትያ 5:18-22 በጽድቅ ንቁ ኃጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። 1 ቆሮንቶስ 15:34 የእምነት የተስፋና የፍቅር ህይወት ባለን ላይ እንጨምር2ኛ የጴጥሮስ 1: 3-8
3 የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 4 ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። 5 ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ 6 በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ 7 እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። 8 እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና:: |
የሕሁድ ትምህርት ከሳምንት በፊት ይወጣል። ሳምንቱን ተዘጋጅተንበት እንምጣ።
የአገልጋዮች ጉባኤ
December 2024
Categories |