ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ
ገላ 4፡4 የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። ዘፍ 12፡3 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ኢሳያስ 7፡14 ሉቃስ ምዕራፍ አንድ፥ 26 በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ 27 ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ። 28 መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። 29 እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና። ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች። 30 መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። 31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። 32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም። 34 ማርያምም መልአኩን። ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው። 35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት። መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። ሉቃስ ምዕራፍ ሁለት 8 በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ። 9 እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ። 10 መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ 11 ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። 12 ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። 13 ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ። 14 ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ። 15 መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው። እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ። በመንፈስ ተሞሉ/ መንፈስ ይሙላባችሁ ኤፌሶን 5:18
አወያይ ወንድም ጌታቸው ሰው ማደሪያ ነው ለባዶነት ሳይሆን ለሙላት ተፈጥሮአል ። ሰው በፈቃዱ ቤተመቅደስ ለመንፈስ ቅዱስ ወይም ተራ ማደሪያ ከአለም ከሰይጣን ከስጋ ለሚመነጩ ነገሮች ይሆናል። በመንፈስ መሞላት ምንድን ነው? ዮሐንስ 4:24 ሉቃስ 4:17-19 መቀባት መሞላት ለምን? 1 ጴጥሮስ 1:15-16 | 2 ጴጥሮስ 1:5-8 እርሱን እንድንመስለው ሐዋ. ሥራ 1:8 ለመመስከር 1 ቆሮንቶስ 12:7 መንፈስ ቅዱስን ለመግለጥ 1 ተሰሎንቄ 5:23 - እንድንቀደስና ያለነቀፋ እንድንሆን 1 ቆሮንቶስ 12:9-11 በስጦታዎች ለማገልገል ገላትያ 5:22-23 ፍሬ እንዲኖረን ዮሐንስ 14:17 እንድናውቀው መሞላት እንዴት? 1 ቆሮንቶስ 2:11 መንፈስ ከመንፈስ ጋር ህብረት በማድረግ ራዕይ 3:20 የልብን በር መክፈት ወይም ፈቃደኛ መሆን ዮሐንስ 7:37-39 ወደ እርሱ በንስሀ መምጣት ማመን መቀበል መሞላት መቸ? ኤፌሶን 5:18 ሁልጊዜ የመሞለት ውጤቱ በጥቂቱ ሐዋ. ሥራ 2:4 አንደበት በመንፈስ ቁጥጥር ስር ሐዋ. ሥራ 4:31 ቃሉን ያለፍርሀት መግለጥ ኤፌ 5:19-20 ምስጋና ዜማ ቅኔ ሮሜ 8:16 መንፈስ ቅዱስ ለመንፈሳችን በመመስከሩ ፊልጵስዩስ 2:13 መፈለግንም ማድረግንም እንድንችል ማድረጉ በረከት ይብዛላችሁ! የድል ህይወት እግዚአብሔር አብ የሰጠን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የተገለጠ፤ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የሚኖር ህይወት ነው::
አብ ሰጠን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድልንሁል ጊዜ ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ድል የእግዚአብሔር ስጦታ ነው 1ኛ የዮሐንስ መልእክት1፥1 ጌታ ኢየሱስ ተገለጠ ፩) ተገለጠ የዳቢሎስን ስራ አፈረሰ የዮሐንስ ወንጌል 16:33 ፪) ሃጢያትን ኮነነልን ሮሜ 8፤3 ፫) ከሃጢያት ነጻ አወጣን 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:9 ፬) በደሙ ህሊናችን አነጻልን ወደ ዕብራውያን 9:14 ፭) ስልጣን አገኘን የሉቃስ ወንጌል 10:20 የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በመንፈስ ሙላት የሚኖር ህይወት የድል ህይወት መሆኑን ባለፈው ጊዜ አይተናል። በመንፈስ ተመላለሱ፥ ገላትያ 5:16፤ የጌታ መንፈስ እርዳታ ሮሜ 8:26 በድል የሚኖሩ ደቀ መዝሙሮች ፩) አለምን ያሸነፈው እምነታችን 1ኛ ዮሐንስ 5:4-5 ፪) በጌታ መኖር 1ኛ የዮሐንስ 2:22-24 ፫) ፍቅርን አውቀን በፍቅር መኖር 1ኛ ዮሐንስ 3:16-24 ፬) ፍቃደኛ መሆንና መታዘዝን ትንቢት ኢሳይያስ 1:19-20 ፭) በመንፈስ መመላለስ/መመራት ወደ ገላትያ 5:18-22 በጽድቅ ንቁ ኃጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። 1 ቆሮንቶስ 15:34 የእምነት የተስፋና የፍቅር ህይወት ባለን ላይ እንጨምር2ኛ የጴጥሮስ 1: 3-8
3 የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥ በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ። 4 ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን። 5 ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ 6 በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ 7 እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ። 8 እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና:: Master Life ትምህርት ስድስት ስሜቶችን መቆጣጠር ስሜቶች፦ በሕይወታችን ለሚገጥሙን ነገሮች የምንሰጠው አስተያየት/ምላሽ (ደስታ፣ ሀዘን፣ ፍቅር፣ ጥላቻ፣ ቁጣ፣ ፍርሃት፣ ትዕግስት፣ ሰላም፣ ስጋት -----) የመወያያ ሀሳቦች - አወያይ ወንድም ጸጋዬ ስሜቶቻችንን ለመገንዘብና ለመቆጣጠር
** እውነት -> እምነት -> ስሜት **
የሕይወታችን ቅደም ተከተል የቃሉን እውነት በማወቅ --> ያወቅነውን እውነት በማመን --> ስሜታችንን እናስገዛ። Master Life ትምህርት አምስት ሰውነትን ለእግዚአብሔር ማቅረብ የመወያያ ቃላት:- 1. ክርስቶስ ነፃ አወጣኝ -
ሮሜ 8:3; ሮሜ 6: 6-7; ሮሜ 8: 11-13 2. የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ 1 ቆሮ 6: 19-20 - ኃይል የሚሰጠኝ ሮሜ 6: 6 - ______ ለማጥፋት ተሰቀለ ቆላስይስ 3: 3-5 - ሞቻለሁ 3. እራስን ማቅረብ ሮሜ 12: 1 4. በዕለት ተዕለት ኑሮዬ አካሌ እንዴት ጌታን ያክብር? ምሳሌ:- አንደበቴ/ምላሴ? ጆሮዬ? ዓይኔ? ***አካሌ በጌታ የተዋጀ እርሱንም ለማክበር የሚውል ነው::*** Master Life
ትምህርት አራት አእምሮህን አድስ የመወያያ ቃላት:- 2ቆሮንቶስ 5: 17 አእምሮን ማደስ (ዓለምን አንምሰል) - ሮሜ 12:2 አእምሮን እንማርክ - 2ቆሮ 10:2 ምን እናስብ? ፊልጵ 4:8; 2:5-8 አእምሯችን እንዴት ይታደሳል - ዮሐንስ 16:13 SUNDAY SCHOOL @ 10 AM The Pursuit We hold these truths to be self-evident, that all men are created equal, that they are endowed, by their Creator, with certain unalienable rights, that among these are life, liberty, and the pursuit of happiness. - (USA Constitution) You, God, are my God, earnestly I seek you; I thirst for you, my whole being longs for you, in a dry and parched land where there is no water. - Psalm 63:1 Though the fig tree does not bud and there are no grapes on the vines, though the olive crop fails and the fields produce no food, though there are no sheep in the pen and no cattle in the stalls, yet I will rejoice in the Lord, I will be joyful in God my Savior.
Habakkuk 3:17-18 Consider it pure joy, my brothers and sisters, whenever you face trials of many kinds, because you know that the testing of your faith produces perseverance. Let perseverance finish its work so that you may be mature and complete, not lacking anything. James 1:2-4 For the kingdom of God is not a matter of eating and drinking, but of righteousness, peace and joy in the Holy Spirit, Romans 14:17 Rejoice in the Lord always. I will say it again: Rejoice! Philippians 4:4 Though you have not seen him, you love him; and even though you do not see him now, you believe in him and are filled with an inexpressible and glorious joy, for you are receiving the end result of your faith, the salvation of your souls. 1 Peter 1:8-9 You make known to me the path of life; you will fill me with joy in your presence, with eternal pleasures at your right hand. Psalm 16:11 |
የሕሁድ ትምህርት ከሳምንት በፊት ይወጣል። ሳምንቱን ተዘጋጅተንበት እንምጣ።
የአገልጋዮች ጉባኤ
December 2024
Categories |