ቅዱስ ቁርባን፥ ለውይይት የቀረበ። አወያይ ፀጋዬ ሉቃስ 22
13 ሄደውም እንዳላቸው አገኙና ፋሲካን አሰናዱ። 14 ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ጋር በማዕድ ተቀመጠ። 15 እርሱም። ከመከራዬ በፊት ከእናንተ ጋር ይህን ፋሲካ ልበላ እጅግ እመኝ ነበር፤ 16 እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው። 17 ጽዋንም ተቀበለ አመስግኖም። ይህን እንካችሁ በመካከላችሁም ተካፈሉት፤ 18 እላችኋለሁና፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከአሁን ጀምሮ ከወይኑ ፍሬ አልጠጣም አለ። 19 እንጀራንም አንሥቶ አመሰገነ ቆርሶም ሰጣቸውና። ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት አለ። 20 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ። ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው። ቅዱስ ቁርባን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች፡- ማቴዎስ 26፡26-29፣ ማርቆስ 14፡22-25፣ ሉቃስ 22፡14-20 ዮሐ 6:52-63 ሐዋ 2:42 ሐዋ 20:7, 1ኛ ቆሮንቶስ 10 : 16-17 እና በ1ኛ ቆሮንቶስ 11:17-34 መጠሪያ ስሙ ፡-
ከላይ የተዘረዘሩት መጠሪያ ስሞች የአንዱ ስርአት መገለጫ ሲሆኑ በህብረታችን የቅዱስ ቁርባን የሚለውን በመጠቀም ስርአቱን የምናከናውን ይሆናል። በቀደመችው ቤተክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን /የጌታ እራት/ በአማኞች ቤት ብዙ ጊዜ ይከበር ነበር (ሐዋ. 2፡46፣ 1ቆሮ 11፡20-22) ። ዛሬ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በተሰበሰበው ጉባኤ ላይ በብዛት ይስተዋላል። ነገር ግን፣ በአግባብና በሥርዓት እስከተከናወነ ድረስ፣ በሌሎች ተገቢ ዝግጅቶች ሊከበር ይችላል (1ኛ ቆሮ 14፡40) ። Comments are closed.
|
የሕሁድ ትምህርት ከሳምንት በፊት ይወጣል። ሳምንቱን ተዘጋጅተንበት እንምጣ።
የአገልጋዮች ጉባኤ
December 2024
Categories |